የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር የድህረ ምርጫ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ።
ሰኔ 15/2018 የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት
የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር ለዞኑ ሕዝብና ለመላው የፓርቲው አባላት የድህረ ምርጫ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ።
ያጋጠሙ ፈተናዎችን በፅናት ተሻግሮ፣ በአንድነት ዜማ አሸብርቆ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ለጻፈው ውድና ለተከበረው የስልጤ ኩሩ ሕዝብ፣ ለፓርቲያችን አባላት፣ ደጋፊዎች፣ አመራሮች፣ እጩዎች፣ ታዛቢዎች፣ ወኪሎች እንዲሁም ብሩህ ተስፋ ሰናቂ ለሆናችሁ የዞናችን ወጣቶችና ሴቶች በግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው ታሪካዊ ምርጫ ላይ ያሳያችሁት ወደር የለሽ ፍቅር፣ የማይናወጥ ቁርጠኝነትና ለከፈላችሁት መስዋዕትነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ክብርት ወ/ሮ ነኢማ አክለውም በምርጫው ሂደት የታየው ትጋት የሕዝቡን የዴሞክራሲ ብስለት ያሳየ መሆኑን ጠቅሰው የተመዘገበው አንጸባራቂ ስኬት ለአላማው የፀና እና ላመነበት ጉዳይ በምንም መልኩ የማይበገረውን በየደረጃው ያለው የአመራራችን እውነተኛ ፅናትና ትግል በተግባር የተረጋገጠበት እንደነበረ ገልፀዋሉ።
ወ/ሮ ነኢማ አያይዘውም ይህ ስኬትና ታላቅ ድል የተወሰኑ መሪዎች የብቸኝነት ልፋትና ውጤት ሳይሆን ይልቁንም በፈገግታችሁ ውስጥ የነበረው ብሩህ ተስፋ፣ በውስጣችሁ የነበረው የማይናወጥ ፅናት እና በልባችሁ ውስጥ የሰረፀው የጋራ እምነት የወለደው በየደረጃው የሚገኘው አመራርና አባል አንጸባራቂ ድል ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ለዚህ ታላቅ ድልና ስኬት በተለይ የሁሉንም መዋቅር ሰብሰብ አድርጎ በመያዝ ከመረጃ ቅብብሎሽ ጀምሮ ዬትኛውም አይነት ችግር እንዳይፈጠር የፓርቲው አመራሮች ተናቦና ተቀናጅቶ የሰሩበት መንገድ አስተዋጽኦ፣ በሕዝቡና በፓርቲው መዋቅር ውስጥ ለነበረው የማይበገረው ፅናትና ለታየው ታላቅ የሀገር ፍቅርና ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የተጎናጸፍነው ድልና ስኬት የሚያስደስተን ብቻ ሳይሆን በትከሻችን ላይ ታላቅ አደራን የሚያኖር ከባድ ኃላፊነት ጭምር ነው ያሉት ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር ፓርቲው ከዚህ ታሪካዊ ድል ማግስት በምርጫ ስኬት ላይ ብቻ እንደማይቆም በመግለፅ ሕዝቡ ያሳየውን የማይናወጥ እምነትና ብሩህ ተስፋ በተጨባጭ የልማት ሥራዎች፣ በመልካም አስተዳደርና በላቀ አገልግሎት በተግባር ለማረጋገጥ ሌት ተቀን ተግተን የምንሰራበት ወቅት ላይ እንገኛለን ሲሉ ገልፀዋል።
በመጨረሻም ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ባስተላለፉት መልዕክት እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ ልብ ለልብ ተገናኝተን ይህንን ታሪካዊ ስኬት ለማየት ስላበቃን በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩኝ አሁን ፊታችንን ሙሉ በሙሉ ወደ ልማት፣ ወደ ማኅበረሰብ አገልግሎት እና ወደ ሕዝባችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት አዙረናል ብለዋል።
የጋራ ጥረታችን ፍሬ አፍርቷል፣ የሰላም እና የልማት ድምፅ አሸንፏል ውድና ኩሩው የስልጤ ሕዝብ ሆይ! በዚህ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ ኢትዮጵያችን በልጆቿ ፅናትና ብስለት ዳግም አሸንፋለች።
አሁን ከፊታችን የቀረው ትልቁ ሥራ በምርጫው ወቅት ያሳያችሁትን የአንድነት ዕሴት በማጠናከር፣ ልዩነቶቻችንን በውበትና በአንድነት አሳምረን፣ ውድ ሀገራችንንና ውብ ዞናችንን በጋራ መገንባት ይጠበቅብናል ሲሉ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ አሸንፋለች፣ ኑ በአንድነት ሀገራችንን እናልማ!" በማለት መልዕክታቸውን አጠቃልለዋል።

















































