"ሁለንተናዊ ብልፅግና ለኢትዮጵያ ልዕልና"

የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንጻ

የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንጻ

መደመር መንገዳችን፤ ብልፅግና መዳረሻችን

በ2017 ዓመታዊ አፈጻጸም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የተበረከተ የዕውቅና ሽልማት።

በ2017 ዓመታዊ አፈጻጸም ከፍተኛና የላቀ ውጤት በማስመዝገብ፣ በክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የተበረከተ የዕውቅና ሽልማት።

መደመር መንገዳችን፤ ብልፅግና መዳረሻችን

የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በ2017 ዓመታዊ አፈጻጸም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የተበረከተ የዕውቅና ሽልማት።

የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በ2017 ዓመታዊ አፈጻጸም ከፍተኛና የላቀ ውጤት በማስመዝገብ፣ በክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የተበረከተ የዕውቅና ሽልማት።

"ሁለንተናዊ ብልፅግና ለኢትዮጵያ ልዕልና"

የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

የገጠር ኮሪደር ስራዎች በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ወራበት ሻማ ቀበሌ

ኮሪደር ልማት ኢንሼቲቭ

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ኢኒሼቲቭ የተገነባ የገጠር ኮሪደር ልማት በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ወራበት ሻማ ቀበሌ

መደመር መንገዳችን፤ ብልፅግና መዳረሻችን

የወራቤ ኮሪደር ልማት አጀማመር

የወራቤ ኮሪደር ልማት አጀማመር

"ሁለንተናዊ ብልፅግና ለኢትዮጵያ ልዕልና"

የመቻቻል አቅም

"ህብረ ብሔራዊነት " "ለህብረ ብሔራዊ አንድነት"

"ሁለንተናዊ ብልፅግና ለኢትዮጵያ ልዕልና"

ክቡር አቶ አደም ፋራህ

"የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ በሁልባራግ ወረዳ ወራበት ሻማ ቀበሌ በመገኘት የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ተመለከቱ።"

መደመር መንገዳችን፤ ብልፅግና መዳረሻችን

የተሞክሮ ልውውጥ

ከጋምቤላ ክልል ለመጡ እንግዶች የተደርገ የተሞክሮ ልውውጥ

የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር መልዕክት

Ethiopia diversity ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሃነት ውብ ተምሳሌት ናት። የተለያዩ ማንነቶች፣ እምነቶች፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና የፖለቲካ አመለካከቶች በአንድነት የደመቁባት ታላቅ ምድር ናት ዜጎቿ በልዩነቶቻቸው ሳይከፋፈሉ፣ ልዩነታቸውን የውበታቸውና የጥንካሬያቸው መገለጫ አድርገው፣ በመከባበርና በመቻቻል ለዘመናት አብረው ኖረዋል። ውድ ህይወታቸውን በመሥዋዕትነት በመክፈልም የሀገራቸውን ሉዓላዊነትና ነፃነት አስከብረው ለእኛ አስረክበውናል።

ነገር ግን ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ የተፈጠሩ የተዛቡ ትረካዎችና የፖለቲካ አመለካከቶች ይህንን የጋራ እውነታችንን ለመሸርሸር ሞክረዋል። አባቶቻችን የሀገር ምሰሶ ያደረጓቸውን እሴቶች የጥንካሬ ሳይሆን የድክመት ምንጭ ለማድረግ የሰሩ ኃይሎች ጥቂት አይደሉም። አልፎ ተርፎም፣ በተለያዩ ጊዜያት የተነሱ አንዳንድ የፖለቲካ ኃይሎች በችግሮች ላይ ቤንዚን በመጨመር መከራችንን ሲያራዝሙት፣ ሌሎቹ ደግሞ ግልጽ ያልሆኑ መፍትሔዎችን በመስጠት ችግሩን ይበልጥ ሲያወሳስቡት ቆይተዋል። የሀገራዊ ለውጡ ፈናጣቂ የሆነው የብልጽግና ፓርቲ ግን የሀገራችንን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በዘላቂነት መፈወስ የሚቻለው በአገራዊ አንድነትና በወንድማማችነት/እህትማማችነት ማዕቀፍ ውስጥ ብቻ እንደሆነ በፅኑ ያምናል። ለዚህም ነው አገራዊ አንድነታችንን በሕግ፣ በአሠራርና በተቋም ደረጃ የትኩረታችን ማዕከል ያደረግነው።

 በዚህ ታላቅ ጉዞ ውስጥ የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በዞኑ ነዋሪዎች የተጣለበትን ታሪካዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። ባለፉት አምስት ዓመታት የሰላም ሰገነት በሆነችው በስልጤ ዞን የኢትዮጵያ ብልፅግና የማይቀለበስ መሆኑን ያረጋገጡ አበይት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ድሎችን አስመዝግበናል በወራቤ ከተማችንም ደማቅ የብልጽግና አሻራ አኑረናል። እርግጥ ነው በጉዟችን ላይ ፈተናዎች አጋጥመውናል። ሆኖም እኛ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ፣ አቅማችንን ወደ ላቀ ውጤት፣ ተግዳሮቶችንም ወደ ታላቅ ስኬት በመቀየር በመተሳሰብና በወንድማማችነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ታላቋን ኢትዮጵያን ብሎም ውዱን የስልጤን ሕዝብ ከፍ ለማድረግ በፅናት ወደፊት ተጉዘናል ጉዟችንንም እንቀጥላለን!" በዞናችን በየደረጃው የምትገኙ የፓርቲያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም መላው ማህበረሰብ የውስጥ አንድነታችንን ይበልጥ በማጠናከር ድህነትን፣ ስንፍናን፣ ሌብነትንና ሙስናን በቆራጥነት በመታገል የድካማችን ማማ፣ የልፋታችን ውጤት የሆነውን ሁሉን አቀፍ ብልፅግናን ማረጋገጥ የምንችለው በዚህ ትግል ነው። በዚህ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ የዞናችን ነዋሪዎች እንደ ሁልጊዜው የጽናት አለኝታችንና የጉዟችን ደጋፊዎች ሆናችሁ ከጎናችን እንደምትቆሙ ሙሉ እምነት አለን። በመጨረሻም፣ ለዴሞክራሲያችን መጎልበት የማይተካ ሚና ያላችሁ ተፎካካሪ የፖሎቲካ ፓርቲዎች ለታላቋ ኢትዮጵያና ለክቡር ሕዝቧ ብልፅግና ሲባል በትብብርና በጋራ እንድንቆም ጥሪዬን አቀርባለሁ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት፣ ፍቅርና ልፋት ትበለጽጋለች!

                                                                                                            አመሰግናለሁ!"

በስልጤ ዞን ባለፉት ዓመታት ወጣቱን ማዕከል ያደረጉና የትውልድ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ስትራቴጂካዊ የልማት ሥራዎች መከናወናቸው ተገለፀ።

በስልጤ ዞን ባለፉት ዓመታት ወጣቱን ማዕከል ያደረጉና የትውልድ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ስትራቴጂካዊ የልማት ሥራዎች መከናወናቸው ተገለፀ።

ግንቦት 01/2018 ከታላላቅ የልማት ግቦች በመነሳት የወጣቱን ተሳትፎና የትውልድ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ተግባራት በዞኑ ውጤታማ በሆነ መልኩ መከናወናቸው ተገለጸ።

ይህ የተገለፀው በዛሬው ዕለት በስልጤ ዞን ባለፉት 8 ዓመታት የለውጥ ጉዞ የጋራ ጥረት ለጋራ ስኬት በሚል መሪ ቃል በወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በመጡ ለውጦች ላይ በወራቤ ከተማ የውይይት መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ስልጤ ለዚህ ደረጀ እንዲደርስ ኣባት እናቶች ያደረጉት ተጋድሎ ከፍተኛ መሆኑን አንስተው በዞኑ ከትልቅ ሀሳብ የመነጨ የወደፊት የትውልድ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራው የዞን አስተባባሪ አካል የዒድ አል-ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አከናወኑ።

በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራው የዞን አስተባባሪ አካል የዒድ አል-ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አከናወኑ።

                 ወራቤ፣መጋቢት 9/2018  የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት

በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ቡድን፣ የዘንድሮውን የዒድ አል-ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አከናወኑ።

በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ለበዓል ማክበሪያ የሚሆኑ የበግ ሙክቶች፣የዱቄት እና ሌሎች መሰረታዊ የምግብ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርገዋሉ።

የወራቤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመረቀ።

የወራቤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመረቀ።

ወራቤ፣ ግንቦት 26/2018 በወራቤ ከተማ የተገነባው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫው ወደ ስራ መግባት በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጡ ተመጋጋቢና ተያያዥ አገልግሎቶችን በተቀናጀ አኳሃን በማቅረብ የተገልጋዩን ጊዜና ወጪ በመቆጠብ ውጤታማነትን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተገልጿል።

በወራቤ ከተማ ከ1.25 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የልማት ፕሮጀክቶች በይፋ ተመረቁ፦

በወራቤ ከተማ ከ1.25 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የልማት ፕሮጀክቶች በይፋ ተመረቁ፦

ወራቤ ግንቦት 14/2018ወራቤ ከተማ አስተዳደር ከ1.25 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን በርካታ የልማት ፕሮጀክቶችን በይፋ አስመርቋል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ጊስት ሙፈሪያት ካሚል ባስተላለፉት መልዕክት ሀገሪቱ በአስቸጋሪ የውስጥና የውጭ ጫናዎች ውስጥ ብትሆንም በርካታ የልማትና የዲሞክራሲ ድሎችን ማስመዝገብ መቻሏን ገልፀዋል።

ያለፉት የለውጥ አመታት የፖለቲካና የተቋም ግንባታ የተሰራባቸው ትልልቅ ስኬቶች የተመዘገቡባቸው ዓመታት ናቸውም ብለዋል

በወራቤ ከተማ የተከናወኑ ፕሮጀክቶች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የወንዝ ዳርቻና ፓርኩ ግንባታ ለከተማዋ ህብረተሰብ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልፀዋል።

የወራቤ የሀይል ማከፋፈያ ጣቢያ መንግስት የህዝብ ፍላጎቶችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ያለውን የላቀ ቁርጠኝነት ያረጋገጠበት መሆኑ ተገለጸ።

የወራቤ የሀይል ማከፋፈያ ጣቢያ መንግስት የህዝብ ፍላጎቶችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ያለውን የላቀ ቁርጠኝነት ያረጋገጠበት መሆኑ ተገለጸ።

ግንቦት 14/2018 ዓ.ም በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በ 640 ሚሊየን ብር የተገነባው የወራቤ ዘመናዊ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የኢፌዴሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ጊስቲት ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና የማህበረሰብ ተወካዮች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ  አሸብር ባልቻ (ኢ/ር) እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
 
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት ጊስቲት ሙፈሪያት ካሚል ፕሮጀክቱ የለውጡ መንግስት የህዝብን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመፍታት ከወሰደው ቁርጠኝነት መነሻ የተገነባ መሆኑን ተናግረዋል።

በስልጤ ዞን በ7ኛዉ ሀገራዊ ና ክልላዊ ምርጫ የቡና ጠጡ እና እጩዎችን የማስተዋወቂያ መርሃግብር

በስልጤ ዞን በ7ኛዉ ሀገራዊ ና ክልላዊ ምርጫ የብልጽግና ተመራጮች የቡና ጠጡ እና እጩዎችን የማስተዋወቂያ መርሃግብር

የፓርቲ ተቋም ግንባታን በማጠናከር በፓርቲው መሪነት የሚፈጸሙ የህዝብን የልማት እና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄን የሚመልሱ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን፡- ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር

የፓርቲ ተቋም ግንባታን በማጠናከር በፓርቲው መሪነት የሚፈጸሙ የህዝብን የልማት እና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄን የሚመልሱ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን፡- ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር

           ታህሳስ 27/ 2018 ዓ.ም
የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት

የፓርቲ ተቋም ግንባታን በማጠናከር በፓርቲው መሪነት የሚፈጸሙ የህዝብን የልማት እና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄን የሚመልሱ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ሲሉ የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የዞኑ ዋና የመንግሥት ተጠሪ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር ገለፁ።

ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት
የ2018 የሁለተኛ ሩብ ዓመት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በወራቤ ከተማ በካሄዱበት ወቅት ነው።

በየደረጃው ያለው የፓርቲ መዋቅር ከምርጫ ማግስት ወደ መደበኛ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ ትኩረት ሊያደርግ ይገባል :- ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር

በየደረጃው ያለው የፓርቲ መዋቅር ከምርጫ ማግስት ወደ መደበኛ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ ትኩረት ሊያደርግ ይገባል :- ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር

                         ሰኔ 15/2018  የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት
በየ ደረጃዉ ያለዉ የፓርቲ መዋቅር ከምርጫ ማግስት ወደ መደበኛ የፓርቲ ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የህዝቡን የልማት እና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ ርብርብ ማድረግ እንዳለበት የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር ገለፁ።

የቅርብ ጊዜ ዜና| Latest News

በስልጤ ዞን ባለፉት ዓመታት ወጣቱን ማዕከል ያደረጉና የትውልድ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ስትራቴጂካዊ የልማት ሥራዎች መከናወናቸው ተገለፀ።

በስልጤ ዞን ባለፉት ዓመታት ወጣቱን ማዕከል ያደረጉና የትውልድ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ስትራቴጂካዊ የልማት ሥራዎች መከናወናቸው ተገለፀ።

በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራው የዞን አስተባባሪ አካል የዒድ አል-ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አከናወኑ።

በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራው የዞን አስተባባሪ አካል የዒድ አል-ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አከናወኑ።

የወራቤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመረቀ።

የወራቤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመረቀ።

በወራቤ ከተማ ከ1.25 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የልማት ፕሮጀክቶች በይፋ ተመረቁ፦

በወራቤ ከተማ ከ1.25 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የልማት ፕሮጀክቶች በይፋ ተመረቁ፦

ወራቤ ግንቦት 14/2018ወራቤ ከተማ አስተዳደር ከ1.25 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን በርካታ የልማት ፕሮጀክቶችን በይፋ አስመርቋል።

አምልጦዎት ይሆን |You May Have Missed

ሚዲያ እና ገጽ| Our Media

አጋሮቻችን I Our Partner