በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራው የዞን አስተባባሪ አካል የዒድ አል-ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አከናወኑ።
ወራቤ፣መጋቢት 9/2018 የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት
በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ቡድን፣ የዘንድሮውን የዒድ አል-ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አከናወኑ።
በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ለበዓል ማክበሪያ የሚሆኑ የበግ ሙክቶች፣የዱቄት እና ሌሎች መሰረታዊ የምግብ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርገዋሉ።
በማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብሩ ላይ የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር ፣የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖሎቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ክቡር አቶ ሁሴን ሱነሞ፣ የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ክቡር አቶ ሳሊያ ሀሰንን ጨምሮ ሌሎች የአመራር አካላት ተገኝተው ድጋፉን አበርክተዋል።
የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በማህበራዊ ዘርፍ ትኩረት ከተሰጣቸው ተግባራት መካከል አንዱና ዋነኛው "ማዕድ ማጋራት" መሆኑን ገልጸዋል። እንደ ስልጤ ዞንም ለዚህ ተግባር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ይህ የበጎ አድራጎት ስራ በበዓል ወቅት አቅመ ደካሞች ያለ ችግር በዓሉን እንዲያሳልፉና የማህበራዊ ትስስሩ እንዲጠናከር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተመላክቷል።

































