በስልጤ ዞን ባለፉት ዓመታት ወጣቱን ማዕከል ያደረጉና የትውልድ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ስትራቴጂካዊ የልማት ሥራዎች መከናወናቸው ተገለፀ።

በስልጤ ዞን ባለፉት ዓመታት ወጣቱን ማዕከል ያደረጉና የትውልድ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ስትራቴጂካዊ የልማት ሥራዎች መከናወናቸው ተገለፀ።

 

ግንቦት 01/2018 ከታላላቅ የልማት ግቦች በመነሳት የወጣቱን ተሳትፎና የትውልድ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ተግባራት በዞኑ ውጤታማ በሆነ መልኩ መከናወናቸው ተገለጸ።

ይህ የተገለፀው በዛሬው ዕለት በስልጤ ዞን ባለፉት 8 ዓመታት የለውጥ ጉዞ የጋራ ጥረት ለጋራ ስኬት በሚል መሪ ቃል በወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በመጡ ለውጦች ላይ በወራቤ ከተማ የውይይት መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ስልጤ ለዚህ ደረጀ እንዲደርስ ኣባት እናቶች ያደረጉት ተጋድሎ ከፍተኛ መሆኑን አንስተው በዞኑ ከትልቅ ሀሳብ የመነጨ የወደፊት የትውልድ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

በሀሳብ በመደጋገፍ ከስህተቶች በመማር እና ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ጉዳይ በጋራ በመስራት ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ለማሳለጥ አባት እናቶቻችን የደረጉትን የትግል ተሞክሮ በመውሰድ በቀጣይም በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በጋራ በመስራት በኩል ወጣቶች የድርሻቸውን ሊወጡ ኢንደሚገባም አሳስበዋል።

መንግስት  ባለፉት የለውጥ ዓመታት አማራጭ እና አካታች የፋይናንስ ስርዓት በማመቻቸት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለመረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ከመስራቱም ባለፈ የእምነት ነፃነት እና ሌሎች መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጠ ፓርቲ ነው ብለዋል።

በዞኑ ማህበረሰቡ ከመንግስት ጋር በቅንጅት የወደፊት ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ በጤናና በትምህርት እንዲሁም በሌሎች የመሠረተ ልማት ስራዎች በትልቅ ሀሳብ ለተሞክሮ የሚሆን ተጨባጭ ስራ መሰራቱንም ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።

በለውጡ መንግስት በዞኑ በከተሞች ዕድገት በኮሪደር ልማት፣በቡና ልማት፣በስራ ዕድል ፈጠራ ፣በመንገድ መሠረተ ልማት በተለይ የሚቶ ቆሼ፣የወራቤ ቦዦባር የመንገድ መሠረተ ልማት ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

መንግስት ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢ በመሆናቸው በሚሰራቸው ሰው ተኮር ስራዎች ላይ በወጣቶች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት ማድረጉን የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው በለፉት አምስት ዓመታት ለ35 ሺህ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መስጠት መቻሉን ተናግረዋል።

የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር በውይይቱ ማጠቃለያ እንደገለጹት መንግሥትና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት ያጋጠሙ ሀገራዊ ጫናዎችን እንደ ዕድል በመጠቀም ወጣቱን ያሳተፉና የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎችን ማከናወናቸውን ገልጸዋል።

በሀገራዊ ፖሊሲዎች መሠረት የዞኑን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራት ተጨባጭ ስኬቶች መመዝገባቸውንም ክብርት  ነኢማ ሙኒር ገልፀዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ጀምሮ መጨረስን መሰረት ያደረገው ራዕይን ሰንቆ በዞን ደረጃ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ በባለቤትነት በጋራ ሲሰራ መቆየቱን አንስተው እንችላለን በሚል እሳቤ ወጣቶች በመፍጠር እና በመፍጠን ሀገርንና አካባቢን በማልማት ቀጣይም ለላቀ ውጤት መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በተለይም ወጣቶች "እንችላለን" የሚል ፅኑ እሳቤን በመሰነቅ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን በማፍለቅና ስራዎችን በዝግጅት ሳይሆን "በመፍጠን" በማከናወን ረገድ ግንባር ቀደም ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባም ክብርት ነኢማ ገልፀዋሉ።

ወጣቱ ትውልድ አካባቢውንና ሀገሩን በማልማት ሂደት ውስጥ ያለውን ጉልበትና እውቀት በሥራ ላይ እንዲያውልም ክብርት ነኢማ አሳስበዋሉ።

በመጨረሻም፣ እስካሁን የተገኙ ስኬቶችን ይበልጥ ለማጠናከርና ለላቀ ውጤት ለመሥራት ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ የገለፁት ክብርት ወ/ሮ ነኢማ በቀጣይ በዞን ደረጃ የሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ መላው የህብረተሰብ ክፍል በተለይም ወጣቶች ከመንግስትና ከፓርቲው ጋር ያላቸውን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ገልፀዋሉ።

በውይይት መድረኩ ላይ ባለፉት በለውጡ ዓመታት በዞኑ የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎች እና በዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶች ላይ የስልጤ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ በድሩ ሱሩር ሰነድ አቅርበዋል።

gallery try zoom