የወራቤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመረቀ።
ወራቤ፣ ግንቦት 26/2018 በወራቤ ከተማ የተገነባው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫው ወደ ስራ መግባት በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጡ ተመጋጋቢና ተያያዥ አገልግሎቶችን በተቀናጀ አኳሃን በማቅረብ የተገልጋዩን ጊዜና ወጪ በመቆጠብ ውጤታማነትን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተገልጿል።
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የትምህርት ቢሮ ሀላፊና የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ክቡር አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካና ሌሎች የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

































