የፓርቲ ተቋም ግንባታን በማጠናከር በፓርቲው መሪነት የሚፈጸሙ የህዝብን የልማት እና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄን የሚመልሱ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን፡- ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር

የፓርቲ ተቋም ግንባታን በማጠናከር በፓርቲው መሪነት የሚፈጸሙ የህዝብን የልማት እና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄን የሚመልሱ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን፡- ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር

           ታህሳስ 27/ 2018 ዓ.ም
የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት

የፓርቲ ተቋም ግንባታን በማጠናከር በፓርቲው መሪነት የሚፈጸሙ የህዝብን የልማት እና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄን የሚመልሱ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ሲሉ የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የዞኑ ዋና የመንግሥት ተጠሪ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር ገለፁ።

ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት
የ2018 የሁለተኛ ሩብ ዓመት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በወራቤ ከተማ በካሄዱበት ወቅት ነው።

ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር በማጠቃለያ መድረኩ ወቅት እንደገለፁ ፓርቲያችን ባላፉት ወራት የህዝቡን ሁለንተናዊ ብልጽግና ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በከናወነው የተቀናጀ ተግባር እንደ ዞናችን በሁሉም ዘርፎች እምርታዊ ውጤቶች ተመዝግበዋል ሲሉም ገልፀዋሉ።

በተለይም የፓርቲውን የፖለቲካ ጤንነት ይበልጥ በማስጠበቅ ‎በህዝብ ዘንድ ቅቡልነቱ የተረጋገጠ የህዝቡን ሠላም፣ ልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በተገቢው መንገድ መመለስ የሚችል ተቋም በመገንባትና በማጠናከር ጠንካራ አደረጃጀት መፍጠር ተችሏል ሲሉም ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር ገልፀዋሉ።

የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በቅርበት ለመመለስ በተኬደው ሪቀት ያህል ውጤቶችን ማስመዝገብ እንደተቻለ የገለፁት ክብርት ነኢማ በተለይም በዞኑ የተረጋጋ የፖሎቲካና የፀጥታ ምህዳር በመፍጠሩ ረገድ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውንም ገልፀዋል።

በዞኑ የተገኙ ስኬቶችን ከማላቅ ጎን ለጎን የአመራርና የአባላት ግንባታ ስራዎችን ከወትሮው ይበልጥ በማጠናከር፣የህብረትና የቤተሰብ ውይይቶችን በሁሉም ደረጃ በማጥለቅ የስርፀት ሥራን ማጠናከርና እንዲሁም የፓርቲያችንን እሳቤዎች የበለጠ ጥልቀት እንዲኖራቸው ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉም ገልፀዋል።

ክብርት ወ/ሮ ነኢማ አክለውም ‎ያለንበት ምዕራፍ በመደበኛ ዕይታ የምንመራበት ሳይሆን፣ ፈጠራንና ፍጥነትን ይበልጥ ተግባራዊ በማድረግ በአዲስ ዕይታና ተነሳሽነት የፓርቲውን ታላላቅ ህልሞች ለማሳካት አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ በንቃት የሚንቀሳቀስበት ወቅት እንደሆነም ገልፀዋሉ።

የውስጠ ፓርቲ ስራዎቻችን በአግባቡ መፈፀምና አጠናክሮ በማስቀጠል ስራዎችን በሁሉም ዘርፍ በተግባርና በአስተሳሰብ ተናቦ በሰከነ አግባብ በመቀናጀት፣ የነባራዊ ሁኔታ ትንተና መነሻ ያደረገ የፖለቲካ ስራ፣ የፓርቲ አደረጃጀቶች በአሰራርና አደረጃጀት መመርያ መሰረት በማደራጀት፣ በማጥራትና የአቅም ግንባታ ስራ በመሰራቱ፣ የወጣቶች፣ የሴቶች፣ የሚዲያ ስራ እና እንድሁም ሌሎችም አቀናጅቶ በማምራት የፓርቲ ተቋም ግንባታን ማስቀጠል ያስፈልጋል ሲሉም ክብርት ወ/ሮ ነኢማ አሳስቧል።

‎የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሁሴን ሱነሞ በበኩላቸው ባለፉት ስድስት ወራት ዞኑን የብልጽግና ተምሳሌት ማድረግ ያስቻሉ ተግባራት መፈጸማቸውን በማንሳት በተለይ በስኬት የታጀቡ ውጤቶችን አጠናክሮ በመሄድ የታዩ ጉድለቶችን በግዜ የለንም መንፈስ አርሞ መሄድ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋሉ።

አቶ ሁሴን አክለውም የፓርቲውን አደረጃጀት በማጠናከርና ጠንካራ ፓርቲ በመፍጠር አሰራርና አደረጃጀቶችን ተከትሎ የሚሄድ ጠንካራ ዕሳቤን ወደ ተግባር ሊቀይር የሚችል ጠንካራ አመራርና አባል ማፍራት ይጠበቅብናል ሲሉም ገልፀዋሉ።

‎የፓርቲውን ቅቡልነት ከምንግዜውም በላይ የሚያሳድጉና የህዝብን ሁለንተናዊ የልማት ፍላጎት ሊያረጋግጡ የሚችሉ ተግባራትን በልዩነት አቅዶ መስራት ያስፈልጋል ሲሉም ገልፀዋሉ።

አቶ ሁሴን አክለውም ተግባራትን በተናጥል ሳይሆን በአደረጃጀት አቀናጅቶ መምራት የህብረተሰቡን ዘላቂ ጥቅም በሚፈለገው ደረጃ ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና እንዳለው አንስተዋል።

‎የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሳሊያ ሀሰን እንደገለፁት የአደረጃጀት ስራዎችን የማጠናከር፣ ችግሮችን ታግሎ የማስተካከልና ተቋማዊ ለውጥን የማረጋገጥ ጉዳይ ለአፍታም መዘንጋት እንደሌለበት አፅንኦት በመስጠት ገልፀዋሉ።

‎አደረጃጀቶቹን በመፈተሽና በማጠናከር ለተልዕኮ ብቁ የማድረግ፣ የአባላት ቅሬታዎችን በማድመጥ በአፋጣኝ ምላሽ የመስጠት፣የገቢ አሰባሰቡን በማዘመን የፓርቲውን አቅም ማሳደግ እንደሚገባም አቶ ሳሊያ ሀሰን ገልፀዋል።

በተለይ ‎የሁኔታ ግምገማን ማጠናከር፣ድንበር ተሻጋሪና ሁለንተናዊ ልማቶችን ሊያሳልጡ የሚችሉ  አስተሳሰቦችን ማጎልበት፣የተቋም ቅንጅታዊ ስራዎችን በመገንባት በሁሉም ስራዎች የወል ትርክትን ማጠናከርና ብልጽግናን በሁሉም ዘርፍ በተግባር ማረጋገጥ ዋነኛ አጀንዳ እንደሆነም አቶ ሳሊያ አንስተዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገመገሙ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና በጉድለት የተነሱ ነጥቦችን አመራሩ በግዜ የለኝም መንፈስ ጠጋ ብሎ ማረም ይኖርበታል  ሲሉም አቶ ሳሊያ ገልፀዋል።

gallery try zoom